Psalms 29

ለማዕበሉ ጌታ የቀረበ ውዳሴ

የዳዊት መዝሙር።

1እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
2ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።

3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤
እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።

4 የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤
የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
5 የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣
ስርዮንንም
አርሞንዔም የተባለው ተራራ ነው።
እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
7 የእግዚአብሔር ድምፅ
የእሳት ነበልባል ይረጫል።
8 የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤
የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9 የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤
ወይም እግዚአብሔር አጋዘን እንድትወልድ ያደርጋል

ጫካዎችንም ይመነጥራል፤
ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።

10 እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤
ወይም ይቀመጣል

እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
Copyright information for AmhNASV